በድሬዳዋ አስተዳደር ላለፉት 18 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት እና የአካባበቢ ጥበቃ ሥራ በዛሬው እለት ተጠናቋል

ከስድስት ሺ ሄክታር በላይ መሬት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ሽፋን ያገኘ ሲሆን ከሀምሳ አምስት ሺ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው ስራ ላይ አርባ ሺ ሜትር ኪዪቢክ አፈር ከመሸርሸር ማዳን ተችሏል ተብሏል።

በመዝጊያ መርሀ ግብሩ ላይ በዋሂል ክላስተር በለገኦዳ ጉኑን ፈታ ገጠረ ቀበሌ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢብራሂም ዩሱፍ አካባቢው ዝናብ አጠር ስለሆነ ይህ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመዝጊያ መርሀ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፌ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የተገኙ ሲሆን በስራው ላይ ብልጫ ላሳዩ የገጠር ቀበሌዎች የዋንጫ ሽልማትና ለእርሻ ስራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *