ልማታዊ ፋክክር ውስጥ በመግባትና ከፍተኛ የህብረተሰብ ንቅናቄን በመፍጠር በልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ማህበረሰቦች የማይጠፉ

አሻራቸውን በአረንጓዴ ቀለም ፅፈዋል ሲሉ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ገለፁ።

በድሬዳዋ አስተዳደር የተቀናጀ ተፋሰስ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ቀበሌዎች የውሃ መሳቢያ ሞተርና የግብርና መሣሪያዎችን ተሸልመዋል።

በመድረኩ ዶ/ር ቢፍቱ መሃመድ በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬደዋ አስተዳደር ተወካይ ተገኝተዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በድሬዳዋ በዘንድሮው የበጋ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የተራቆቱ አካባቢዎች የለማ መሆኑን ገልፀው።

በተራቆቱ ስፍራዎች ላይ የተጀመረው የተፋሰስ ልማት የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የተጀመሩ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራ ለማሳካት ወሳኝነት አለው ብለዋል።

በተያያዘም የተፋሰስ ልማት ስራው በገጠር የተጀመረውን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ ህብረተሰቡን ከተረጂነት ለማላቀቅ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ ማጠቃለያውን ባደረገው የጀልዴሳ ክላስተር ለገዲኒና ሌሎች ቀበሌዎች የኩሬ ቁፋሮ፣ የመስኖ ካናሎችን ጠረጋ በማከናወን በገጠሩ የተሻለ ምርትና ምርታማነት እንዲፈጠር ህብረተሰቡ ባደረገው የነቃ ተሳትፎ የለገ ዲኒ ቀበሌ አንደኛ የወጣ ሲሆን ጀልዴሳ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ የጭሪሚቲ ቀበሌ ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

ለእያንዳንዳቸው የውሃ መሳቢያ ሞተር እና ለግብርና ስራ የሚሆኑ መሳሪያዎችን ከዶ/ር ቢፍቱ መሃመድ በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬደዋ አስተዳደር ተወካይ እጅ ተረክበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *