1445 ኛው የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ በዛሬው እለት ከሁለት ሺህ በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አሳታፊ ያደረገ ታላቅ የአፍጢር መርሀ-ግብር በዛሬው እለት በለገሀር አደባባይ ላይ ተካሂዷል ።
በዚሁም መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረገቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የ 2016 ዓ.ም የአብይ ጾም እንዲሁም 1445 ኛው የረመዳን ፆም በእኩል ቀን መጀመሩን ተናግረው በዛሬው እለትም በለገሀር አደባባይ ላይ ለተካሄደው ታላቅ የኢፍጣር መርሀ-ግብር አዘጋጆች ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በዚሁም የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላይም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ተሳታፊ ከመሆናቸውም በዘለለ የአስተዳደሩ ክፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።


