በድሬዳዋ የወረዳ 03 አስተዳደር እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የድሬዳዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን የዓብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ ለእምነቱ ተከታዮች በዛሬው እለት የታሸጉ ውሀዎችን እና ጣፋጭ ምግቦችን ሰተዋል ።
በዛሬው እለት በድሬዳዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን የዓብይ ፆምን ፆመው ለወጡ የእምነቱ ተከታዮች የተደረገው የታሸጉ ውሀዎች እና ጣፋጭ ምግቦችን የመስጠት መርሀ-ግብር ድሬዳዋ የምትታወቅበትን በጋራ ተቻችሎ ተከባብሮ እና ተዋዶ የመኖር እሴትን በጉልህ የሚያሳይ መሆኑን የ 03 ወረዳ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆነው አ\ቶ ምትኩ ሁነኛው ተናግረዋል ።
የተለያዩ እምነቶች እና ብሔሮች ተቻችለውና ተከባብረው በፍቅር በሚኖሩባት ድሬዳዋ ላይ በዛሬው እለት የዓብይ ፆምን ለሚፆሙ የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆኑ እህት ወንድሞቻችን የታሸጉ ውሀዎች እና ጣፋጭ ምግቦችን ከወረዳ 03 አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን መስጠታቸውን አቶ አብዲ ኢብራሂም ወይም አብዲ ኢብራሂም ተናግሯል ።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አባላትም ተሳታፊ ሆነዋል ።


