የአብይ ፆምና_የታላቁን_የረመዳን አጿማትን ምክንያት በማድረግ ህይወታቸዉ ያለፈ ሰራተኛችን እና እረጅም አመታትን በተቋሙ ያላገለገሉ ባለዉለታዎች ያሰበ ቤተሰባዊ ጥየቃና ድጋፍ ተደረገ ።

ይሄዉ የድ/ዳ ፍትህ ፀጥና ህግ ጉዳዮች ቢሮ እንደ ተቋም የጀመረዉ ቤተሰባዊ ጥየቃ ድጋፍና አብሮነት በአጿማቱ የፍቺ በዓላት ወቅትና በመደበኛ ግዜያት የሚቀጥል ስለ መሆኑም ተገልፆል።

የታላቁ ረመዳንና የአብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ የድሬደዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ በተቋሙ በአመራርነትና በባለሞያነት ሲያገለግሉ የቆዩና በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸዉ ያለፈ እንዲሁም እረጅም ግዜያትን ያገለገሉ ቀደምት የተቋሙ ባለዉለታወዎችን በመማሰብ በመጀመሪያ ዙር በቢሮዉ ሃላፊ የተመራ የአመራርና ሰራተኛ ተወካዮች በመኖሪያ ቤታቸዉ በመገኘት ቤተሰባዊ ጥየቃ አካሂደዋል፡፡

በእዚሁ ቤተሰባዊ ጥየቃ ላይ የተገኙት የድሬደዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አብደሰላም አህመድ በቅድሚያ እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን ቀጥለዉም በሞት ያጣናቸዉ የስራ ባልደረቦቻችን ዛሬ ላይ ከእኛ ጎን ቢለዩሙ ሁልግዜም ስናስባቸዉና ስናሰታዉሳቸዉ እንኖራለን ያሉ ሲሆን በቀጣይም ይህም መሰሉ ቤተሰባዊ ጥየቃና ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቤተሰባዊ ጥየቃ የተኬደባቸዉ ቤተሰቦች በኩላቸዉ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞ በመኖሪያ ቤታቸዉ ተገኝተዉ ላደረጉት ጥየቃና ቤተሰባዊ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

#የአብይና_የረመዳን_አጿማትን ምክንያት በመድረግ አመራርና ሰረተኛዉ እርስ በራሱ ብሎም ከሌላዉ ህ/ብ ጋር በመረዳዳትና አንዱ ለሌላዉ በማካፈል የፆም ግዜያቶቹን እንዲያሳልፉ ለማስቻል በማሰብ ቀደም ብሎ የማፍጠሪያ ቴምሮች በቤተሰባዊ አብሮነት ለሰራተኛዉ የተበረከተ ሲሆን አሁን ላይ በተካሄደዉ ቤተሰባዊ ጥየቃ ደግሞ ለፆም ማፍጠሪያ የሚሆኑ የተለያዩ አሊሚ ምግቦችና የምግብ ግበአቶች በድጋፍ ተበርክተዋል፡

ይሄዉ ቤተሰባዊ አብሮነትና ድጋፍ በቀጣይም የአብይ ፆም ፍቺ የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ ቤተሰባዊ ጥየቃና ድጋፎች እንዲሁም በተለያዩ መርሀ ግበሮች የሚቀጥልም ይሆናል፡፡

#የድሬደዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ባሳለፍነዉ የገና በዓል እንዲሁ ከመላ ኢትዮጲያ የተዉጣጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በዓሉን በጋራና አብሮነት እንዲያሳልፉ መአድ በጋራ የመጋራትና ሌሎች የበአል መርሀ ግብሮች ያካሄደ ሲሆን ይህንኑ አብሮነትና ቤተሰባዊነት ይበለልጥ ለማስቀጠል ለኢድ-አልፈጥር በአል መሰል ፕሮግራሞች እንደሚካሄዱም ተገልጻል፡፡ሲል የፍትህ ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *