የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በጋራ በመሆን በቅድስት ማርያም ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን በመገኘት የዓብይ ፆምን ፆመው በስርዓተ ቅዳሴ ለተሳተፉ የእምነቱ ተከታዮች የታሸጉ ውሀዎች እና ጣፋጭ ምግቦችን የመስጠት መርሀ-ግብር በዛሬው እለት አካሄዱ

በመርሀ ግብሩ ሲያስተባብሩ ያነጋገርናቸው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በአብሮነትና በመተሳሰብ የፆም ወቅቱን እያመሰገንን ነው በማለት የተናገሩ ሲሆን፤ የዛሬው ዝግጅት ዋነኛ አላማም በድሬደዋ ሁሉም ሀይማኖት በመከባበርና በመተሳሰብ እንደሚኖር ለማሳየት መሆኑን ጠቁመዋል።

አብሮነትና ፍቅር በተግባር በሚገለፅባት ድሬዳዋ ዛሬም ብዙዎች በተምሳሌትነት ሊወስዱት የሚገባ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በቀጣይም እንደዚህ አይነት የመቻቻልና የአብሮነት እሴትን የሚያጠናክሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስተባባሪዎቹ አመላክተዋል።

እንደዚህ አይነት ፕሮግራም በመዘጋጀቱ መደሰታቸውን የገለፁት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ምዕመናን ሲሆኑ ትንሿ ኢትዮጲያ የሚለውን ስያሜ ያገኘነውም አብሮነትን በተግባር በማሳየታችን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *