የዲጅታል ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአመራር የምዘና ስርዓትን በማዘመን ስራን በውጤት ለመለካት በድሬዳዋ አስተዳደር የተከናወነው ተግባር አበረታች እንደሆነ ተገለፀ ።

በድሬዳዋ አስተዳደር የተከናወኑ የዲጅታል ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአመራር የምዘና ስርዓትን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎችን ልምድ በመውሰድ እና በመቀመር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለፌደራል ተቋማት፣ለሁሉም ክልሎች ና የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ከፌደራል ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የICT ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙላትና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር መስሪያ ቤት የብሄራዊ ኔትዎርክ ማሳለጫ ፕሮጀክት መሪ አቶ ዳንኤል አድነው ወደ አስተዳደሩ የመጡ ሲሆን ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊትም ከብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ ጋር ትውውቅ በማድረግ የመጡበትን ዋንኛ ዓላማ በዝርዝር አብራርተዋል።

የአስተዳደራችንን አመራሮች በመደበኛ ስራዎች በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፓርትና የውስጠ ፓርቲ ስራዎችን በዘመናዊ የምዘና ስርዓት በተቀላጠፈ መንገድ መመዘን መጀመራችን የአመራር የመፈፀም አቅምን ከማሳደጉም በላይ የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት በተያዘላቸው የዕቅድ ዘመን በጥራት እንዲፈፀሙ እና በአግባቡ ያልተፈፀሙ ተግባራቶች ካሉም በአመራሩ ዘንድ የተጠያቂነት ስርዓት እንዲኖር ያስቻለ ስራን በውጤት ለመለካት ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ሲስተም መሆኑንና ይህን ሲስተም ከማዕከል የመጣችሁ ከፍተኛ ባለሞያዎች እንደ ባለሞያ በመፈተሽ በጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ ከታመነበት የፌደራል ተቋማት፣ሁሉም የሀገራችን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ እንዲያደርጉት እንደ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ና እገዛ እንደሚያደርጉና በሲስተሙ ላይ ልምድ ለመውሰድ የመጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች በሚኖራቸው ቆይታ የተሻለ ልምድና ተሞክሮ ይዘው እንደሚሄዱ ሙሉ እምነት እንዳላቸው አቶ አብራሂም ዩሱፍ ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ ላይም በብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ በአስተዳደሩ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሶፍት ዊሮችን በአስተዳደሩ መንግስት ተቋማት ተግባራዊ በማድረግ በሀገር ደረጃ የዲጅታል ብልፅግናውን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ለቡድኑ አስረድተዋል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እንደ አስተዳደር በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርትን የሚያግዝ ሶፍትዌር በማልማት አመራሩን መመዘን መቻሉና አመራሩ በተግባር አፈፃፀም መለካት በመጀመሩ ተቋማት ካቀዱት እቅድ ጋር የበጀት አጠቃቀማቸውን እና እቅዱ መከናወኑን ለመከታተል እና ለመደገፍ የጎላ ሚና አለው ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የኘላን ኮምሽን ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ዳዲ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉት ተሞክሮዎችና ልምዶች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል::

ከማዕከል ለመጡ ቡድኖችም የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ዝግጀት፣ የሀብት አስተዳደርና በጀት ዝውውር አሰራርና አተገባበር ዙሪያ ያሉትን ተሞክሮዋች በዝርዝር ቀርበዋል።

የልዑካን ቡድኑም በአስተዳደሩ በለማው ሶፍትዌር ዙሪያ የቀረበላቸውን ገለፃ ከተከታተሉ በኋላ በሶፍትዌሩ አተገባበር ላይ ቴክኒካል ፍተሻዎችን በማድረግና አጠቃላይ አሰራሮቹን በተመለከተ ዝርዝር ገለፃ ሶፍትዌሩን ባለሙ ባለሞያዎች ከቀረበላቸው በኋላ በቀረበላቸው ገለፃና ባደረጉት የሲስተም ፍተሻ በአስተዳደሩ በለማው የአመራር ምዘና ሶፍትዌር ከጠበቁት በላይ ልምድ መግኘታቸውንና ሲስተሙ እንደ ሀገር አቀፍ በፌደራል ተቋማት፣ ለሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *