የድሬዳዋ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድለእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞቻችን የአፍጢር ፣ ለክርስትና እምነት ተከታይ የአጥቢያችን ምእመናን ከቤተክርስቲያን አስቀድሰው ሲወጡ የውሃና ጣፋጭ ምግቦችን ለማጋራት ስንነሳ በቅድሚያ ወደ ውስጣችን እንመልከት ብለን በሁለቱም ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮችም አብሮነታችንን ለመግለጽ ያደረግነው የመአድ ማጋራት ነው ብለዋል ።
በአፍጢር መርሐ ግብሩ ወቅትም ለዝግጅቶቹ መስመር እና መሳካት በቅንጅት ለሰሩና ላስተባበሩ ሰራተኞች ምስጋና የቀረበ ሲሆን በቀጣይ የየተቋማቱ የስራ እንቅስቃሴና ተግባራት ላይም እንደ መርሐ ግብሩ ስኬት ሁሉ በትጋትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የየተቋማቱ ኃላፊዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የክርስትና እምነት ተከታዮች አብይ ጾምን የእስልምና እምነት ተከታዮች ታላቁን የረመዳን ወር ጾም እየጾሙ ባለበት በዚህ ወቅት በተቋማቶቻችን ውስጥ ላሉ ዝቅተኛ ደመዎዝ ተከፋይ ሰራተኞቻችንን መአድ ማጋራታችን እንደ ሰው የህሊና ሰላም እንደ ሐይማኖት አስተምህሮ ደግሞ የጽድቅ ተግባር ነው ያሉ ሲሆን ያለንን መተሳሰብና አብሮነት ለመግለጽም ጭምር የተደረገ መሆኑን አክለዋል።
የመአድ ተጋሪ ሰራተኞችም ተቋሞቻቸው በዚህ ኑሮ እየከበደ በመጣበት ወቅት አስታውሰው ይሔንን ድጋፍ ላደረጉላቸው ተቋሞቻቸው ያላቸውን ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።


