ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር።
ዘንድሮ የረመዳን ወር እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾም በተመሳሳይ ቀን በመጀመራቸው ፥ ከጥንትም ‘በትንሿ ኢትዮጵያ’ #ድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ እሴት፥ በይበልጥ ደምቆ መታየቱ የማይካድ ሀቅ ነው።
የነገዋ የኢድ ዕለት፥ በረመዳን የጾም ወር የፈፀምናቸውን የአንድነት፥ የእዝነት፥ የመረዳዳት እና ሌሎች በርካታ መልካም እሴቶች አጠንክረን፥ በቀጣይ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ለማስቀጠል ለራሳችን ቃል የምንገባበት ልዩ ቀን ናት።
‘ረመዳን ሙባረክ’ ተባብለን የጀመርነውን የጾም፥ ፀሎት እና ስግደት ወር በሰላም እንድንጨረስ ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና እያቀረብኩ፥ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ ይህ በዓል የፍቅር፥ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ኢድ ሙባረክ


