የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለመላው የእስልምና ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛዉ የኢድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የኢድ አል ፊጥር በዓል ለአገራችንን ሰላም መጎልበት ዱዓ የሚደረግበት፣ የደስታ፣ የዕዝነትና የርህራሄ፣ የመተሳሰብ፣ በተለይም በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ያለው ለሌለው አካፍሎ ሁሉም ወገናችን በደስታ የሚውልበት፣ ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክርበት ዕለት እንዲሆን እመኛለው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 6 የለውጥ አመታት በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሟትም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር ያጋጠሙንን ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር በኢኮኖሚ በፖለቲካና ማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገባችን ከኛም አልፎ ሌሎች የአለም ሀገራት የመሰከሩት ሀቅ ነው።

በዚሁ መሠረት የድሬዳዋ አስተዳደርም እንደ ሀገር የተጣለውን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይ ለማሳካት ድሬደዋን የምስራቋ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ርዕይን በማስቀመጥ ለስኬቱም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በተለይም ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና ፍትሐዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማጠናከር በሚደረገው የተቀናጀ አገራዊ ርብርብ ሁሉም የአስተዳደራችን ነዋሪ ከመንግስታችን ጎን በመሆን የበኩሉን ደማቅ አሻራ እንዲያኖር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም ይህን በሁሉም ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት እና የጋራ ትግል የተገኘውን ድልና ስኬት አስጠብቀን ባሳለፍነው ስድስት የለውጥ ዓመታት ጉዞ ያጋጠሙ እና ወደ ፊትም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ከሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዟችን ሳይገቱን በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ስር በወንድማማችነት፣ በእህትማማችነትና በአብሮነት ለመሻገር፣ በምክክርና በመደማመጥ ሰላምን በማፅናት እንዲሁም የወል ትርክትን ለጠንካራ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ በማዋል እና በሁሉም ዘርፎች የላቀ ድልና ስኬት በማስመዝገብ ለሀገራችን ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን መሆን ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድንወጣ ስል መልዕክቴን እያስተላለፍኩኝ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ

አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ

መልካም የኢድ አል ፊጥር በዓል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *