ድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

የተከበራችሁ የአስተዳደራችን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በአዲስ ምእራፍ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የህብረተሰቡን ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በምክር ቤቱ በተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የአስተዳደሩን አስፈጻሚ አካላትን የስራ እንቅስቃሴ በመከታተል ፣ በመቆጣጠርና አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ ፣ የሰላም ፤ የፍቅርና የመተሳሰብ ተምሳሌት የሆነችውን አስተዳደራችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአስተዳደሩ ህዝብ ከአስተዳደሩ ምክር ቤት ጎን በመቆም ለሰላምና ለዲሞክራሲ መረጋገጥ እያሳየ ስላለው ንቁ ተሳትፎ በራሴና በአስተዳደሩ ምክር ቤት ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የሮመዳን ወር ሲያደርግ የቆየውን ችግረኞችን የመርዳት ሃይማኖታዊ ስረአት አጠናክሮ በማስቀጠል አቅመ ደካሞችን በመደገፍ በአሉን በደስታ እንዲያከብሩ እንድናደርግ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ በአሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ፡፡

ፈቲህያ አደን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *