የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ሀርቢ ቡህ ለኢድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት መልዕክት…….!!

ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ ባለፉት 30 ቀናት በጾምና ጸሎት ማሳለፉን በመጥቀስ የረመዳን ወር ከፈጣሪ ምህረት የሚለመንበት፣ መረዳዳት የሚጠናከርበትና በጎ ተግባራት የሚስፋፋበት ወር በመሆኑ የኢድ በዓልም የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የምናሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክር እለት መሆኑንም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

እስልምናን ጨምሮ ሁሉም ሃይማኖቶች መሰረታቸው ሰላም በመሆኑ በሃይማኖቶቹ ውስጥ ያሉ መልካም እሴቶችን በመጠቀም ለሰላም ሁሉም ዘብ መቆም ይገባልም ሲሉም በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እና አብሮነትና መደጋገፍን በማጎልበት ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በተከተለ መልኩ ማክበር እንደሚገም ጠቁመዋል፡፡

መልካም የዒድ-አልፈጥር በዓል ይሁንልን።!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *