የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ለ1445 ኛውን የኢድ አል-ፊጥር በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ለእናንተ ለወገኖቼ የመልካም ምኞት መግለጫ ለማስተላላፍ በመቻሌ የተሰማኝን ከፍ ያለ ክብርና ልባዊ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡

“በዓሉን ስናከብር የመተጋገዝና አብሮ የመኖር የድሬዳዋ ዕሴቶች ይበልጥ እንዲያድጉ በታላቁ የረመዳን ፆም ያሳያችሁት ፍፁም የመረዳዳት፣ የመደጋገፍና የመከባበር መንፈስ ይጎለብት ዘንድ በአብሮነት ልታከብሩት ይገባል ብለዋል።

በተቀደሰው የረመዳን ወር ለሀገራችሁ ጸጋና በረከት፣ ሰላምና ፍቅር እንደ ጾማችሁና እንደ ጸለያችሁ ሁሉ፥ በክብረ በዓሉም፣ ከዚያ ወዲያ ባሉት ቀናትም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ዱዐ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በዓሉ አብሮነታችን የሚፈካበት የሚያብብበት፣ ሰላምና ሀገራዊ አንድነታችን ስር የሚሰድበት የበረከት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ብለዋል፡፡

መልካም ኢድ አልፈጥር ይሁንላችሁ።!!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *