በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠውና በታላቅ ድምቀት የሚከበረው 1445 ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር ተከበረ ተከብሯል
በአሉንም ለማክበር ከማለዳው 12 ሰአት አንስቶ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተክቢራዎችን እያሰሙ ወደ ኢድ ሰላት መስገጃም አምርተዋል ።
በበአሉ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ የእስልምና መሰረት የሆነው ቅዱስ ቁርአን የወረደበት የወራት ሁሉ ቁንጮ ረመዳን ወር መልካምነት ጎልቶ የሚሰፍንበት ፣ የፈጣሪ ምህረት የሚበዛበት እንዲሁም ይቅር የሚባባሉበት መልካም ወር እንደመሆኑ ሀይማኖቱ በሚፈቅደው መሰረት በፆም በፀሎት ፈጣሪን በማሰብ ፣ ታማኝ በመሆን እና መልካም ተግባራትን በመፈፀም በጋራ በአሉን በኢድሶላት ማክበራቸውን በእለቱ ተናግረዋል ።
የኢድ አልፈጥር በዓል ሲከበር ያለው የሌለውን በመርዳት ፣ በመተጋገዝ እንዲሁም በአንድነት በመሆን በአሉን ማክበር እንደሚገባም ነው የበአሉ ታዳሚዎች የተናገሩት ።


