በዛሬው ዕለት የኮሪደር ልማት ድሬዳዋ ላይ ተግባራዊ በሚደረግበት ነጥቦች ዙሩያ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
የኮሪደር ልማት በተለያዩ አዋጅችና ደንቦች የተቀመጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እንዳልተተገበረ ምክትል ከንቲባው አንስተው፤ የኮሪደር ልማት ድሬዳዋን ለማዘመን ብሎም ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።
በመድረኩ በድሬደዋ አስተዳደር የተመረጡ የከተማ ኮሪደሮችን ለማልማት የተዘጋጀ እቅድ ቀርቦም ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ማጠቃለያም የቀረበው ፕሮፖዛል በጊዜ ወደስራ እንዲገባና ስራዎችም በተቀናጀና በቀደም ተከተል እንዲሰሩ አቶ ሀርቢ አቅጣጫ ሰተዋል።


