በዛሬው ዕለት በሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን የተመራ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
ልኡክ ቡድኑ በጉብኝቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ሁለገብ ወጣቶች ማዕከልን፣ የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ፖርክን፣ ሲቪክ ሴንተርን እንዲሁም የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስታዲየምን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የሱማሌ ብሄራዊ ክልል ም/ ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን አሁን ላይ በድሬደዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙት ግዙፍ ፕሮጀክቶች በሀገር አቀፍ ደረጃም በምሳሌነት የሚቀርቡ ናቸው በማለት ተናግረዋል።
ም/ ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በተሰሩት የፕሮጀክት ስራዎች የአመራሩ ቁርጠኝነት የሚታይ በመሆኑ አመስግነው በዚሁ ይቀጥል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


