በአስተዳደሩ ከ124 በላይ ፕሮጄክቶች እየተተገበሩ ሲሆን በበጀት ዓመቱ እየተከናወኑ ከሚገኙት ውስጥ ለማህበረሰብ ብልጽግና ቅድሚያ የተሰጣቸው ሜጋ ፕሮጄክቶች በተቀመጠላቸው የግንባታ ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ከማድረግ አኳያ በተለየ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል ፡፡
የሲቪክ ማእከል ፣ የወጣቶች አካዳሚና ለተለያዩ ቢሮዎች አገልግሎት እንዲውል ታስቦ እየተገነባ ያለው ባለ አምስት ወለል ህንጻ ፕሮጄክቶች ካቢኔው ሪፖርቱን ካደመጠ በኋላ ተዘዋውሮ የጎበኛቸው ሲሆን ፕሮጄክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ እስካሁን ከነበረው ከቀን በተጨማሪ በለሊት ፈረቃ ጭምር ስራዎችን የማከናወን ልምድ መምጣት እንዳለበት መግባባት ላይየተደረሰ ሲሆን በዚህ አግባብ የ4.2 ኪ/ሜ የአስፓልት መንገድ ግንባታና የሲቪክ ማእከሉ ፕሮጄክቶች ተሰርተው መጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡
ስራን ከቀን ፈረቃ ጋር ብቻ የማማያያዝ ሂደት መለወጥ ይገባዋል ፡፡ በምሽት ፈረቃ የመስራ ባህል መዳበር አለበት ያለው የአስተዳደሩ ካቢኔ ይህም ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባሻገር ጠንካራ የስራ ባህልን ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ፕሮጄክቶች በሳምንት ሁለት ቀን በተቋራጮቹ ሪፖርት እንዲቀርብና እየተገመገመ እንዲፈጸም ፣ የአከፋፈል ሂደቱም በጋራ አካውንት ሊፈጸም እንደሚገባው ካቢኔው አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጄክት አፈጻጸም ልምድን በመከተል ፕሮጄክቶችን በተያዘላቸው የግንባታ ጊዜ ውስጥ በፍጥነት ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡
ፕሮጄክቶች በዘገዩ ቁጥር የዋጋ ማሻሻያ እየተጠየቀባቸው ለሌላ ልማት ሊውል የሚገባው ውስን ሀብት እንዲባክን መንገድ ይከፍታል ያለው ያስተዳደሩ ካቢኔ ተቋራጮች የሚወስዷቸውን ፕሮጄክቶች ግንባታ ከ25 ከመቶና ከዚያ በላይ ሳያከናውኑ የቅድመ ክፍያ የማጸምበት አሰራር ሊተገበር ይገባል ብሏል ፡፡
የወጣቶች አካዳሚ የቀሩትን ስራዎች በፍጥነት በመጨረስ በደንብና በመመሪያ ተዋቅሮ ገቢ ወደ ማመንጨት ሊሸጋገር እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የሲቪክ ማእከሉን ፕሮጄክት የያዘው የውጭ ሀገር ተቋራጭ በፍጥነት ስራውን የሚያጠናቅቅበት ልዩ አቅጣጫ ተሰጥቷል ፡፡


