ወጣቶችን ጨምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ተብለው በተለዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የኤች አይቪ/ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየተነገረ ይገኛል፡፡
በዘንድሮው የአለም ኤድስ ቀን “የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤችአይቪ መከላከል” በሚል መሪ ቃል ህዳር 2016 ዓ.ም ታስቦ መዋሉ ይታወቃል፡፡ ማህበረሰቡ ኤች.አይ.ቪን በመከላከል ረገድ የሚጫወተው የማይተካ ሚና በአገር አቀፍ ደረጃና እስከታች ባለው የመንግስት መዋቅርና በማህበረሰብ አደረጃጀት ዕውቅና የሚሰጥበት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ማህበረሰቡን በማብቃት ወደ መሪነት ደረጃ ለማምጣት እንዲሁም የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ምቹ ሁኔታዎችን የተፈጠሩበት ጊዜ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ማህበረሰቡ በኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም ዕቅድ ዝግጅት፤ ትግበራ፤ ክትትል እና ግምገማ እንዲሁም ሃብት ማሰባሰብና አስተዳደር ላይ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ማስቻል ትልቁ ጥረት ነው፡፡ በቂ እና ቀጣይነት ያለው የሀብት ድጋፍ በማድረግ ማህበረሰቡ በኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም ላይ ያለው የመሪነት ሚና እንዲወጣ ማስቻል ያስፈልጋል፡፡
ማህበረሰቡ በኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም የመሪነት ሚናውን እንዳይወጣ የሚያደርጉ መሰናክሎችን በማስወገድ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች ላይ በስራ ቦታ እና በማህበራዊ ህይወት የሚደርሰዉን የአድሎና መገለልን ማስቀረት ይገባል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት 0.9% ቢሆንም፤ የቫይረሱ ስርጭት ከቦታ ቦታ እንዲሁም ከማህበረሰብ ማህበረሰብ ከፍተኛ ልዩነት ያሳያል፡፡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጾታ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ልዩነትና በተሰማሩበት የሥራ ባህሪያቸው ምክንያት የኤች.አይ.ቪ ተጋላጭነታቸው ይለያያል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት የስርጭቱ ሁኔታ በጾታ ሲታይ 60 % የኤች.አይ.ቪ ስርጭት በሴቶች ላይ ይታያል፡፡ በከተማ ያለዉ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት ከገጠር አንፃር ሲታይ በከተማ ያለዉ የኤች.አይ.ቪ ስርጭት በሰባት እጥፍ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች (PLHIV population) 610,350 (M- 238,853 : F- 371,497) የኤች.አይ.ቪ ስርጭት (Adult HIV prevalence) 0.9% አዲስ በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ሰዎች (New HIV infections) 8,257 ( M – 3,185 F – 5,072 በኤድስ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር (Annual AIDS deaths) – 11,322 ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች (PLHIV population) 11,096 (M- 4,388 : F- 6,708 ) የኤች.አይ.ቪ ስርጭት (Adult HIV prevalence) 2.9% መሆኑን በቅርብ የተጠናው ጥናት ያሳያል፡፡
አዲስ በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ሰዎች (New HIV infections) 244 (M= 100 F=144) በኤድስ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር (Annual AIDS deaths) 307 በ2030 ኤድስን የማቆም ራዕይ ከግብ ለማድረስ አገሮች ስምምነት ተቀብለው መተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀገራችንም ይህንን ራዕይ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ግቦችን አስቀምጣ በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡ የተቀመጡ ግቦችም እ.አ.አ በ2025 ሶስት ዘጠና አምስቶችን ማሳካት ሲሆን፤ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ውስጥ 95% የሚሆኑትን ተመርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ተመርምረው ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የተገኘባቸዉን ሰዎች 95% የሚሆኑትን የጸረ-ኤች.አይ.ቪ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ እና ህክምና ከጀመሩት ሰዎች ውስጥ ደግሞ 95% የሚሆኑትን ህክምናቸውን በትክክል ተከታትለው በደማቸው ውስጥ ያለውን የቫይረስ ልኬት መጠን በዝቅተኛ ደረጃ (≤50 cc/ml) እንዲሆን በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የተመዘገቡ ዉጤቶች የኤችአይቪ በደማቸው ይገኛል ተብሎ ከሚገመቱ ወገኖች መካከል 84 በመቶ የሚሆኑት ተመርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁና ከእነዚህ መካከል 98 በመቶ ያህሉን ደግሞ የፀረ-ኤችአይቪ መድሀኒት ላይ እንዲጠቀሙና መድኃኒት ከሚወስዱት ውስጥ 96.3 በመቶ ያህሉን የቫይረስ ልኬት መጠን በሚፈለገው መጠን እንዲወርድ ማድረግ ተችሏል (2022 HIV spectrium)፡፡
በዓመት ውስጥ የሚኖረውን በኤድስ ምክንያት የሚከሰትን ሞት መጠን በ2010 ከነበረበት 125/100,000 በ2022 ወደ 11/100,000 በማውረድ ከ52 ከመቶ በላይ መቀነስ ተችሏል (2022 HIV spectrium)፡፡ ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ምጣኔ እ.ኤ.አ በ2010 ከነበረበት 46% እ.ኤ.አ በ2022 ወደ 12% በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል (2022 HIV spectrium)፡፡
ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ጥምረት ማህበራት በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞች ዕቅድ፣ ትግበራ፣ ክትትልና ግምገማ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዲያረጉና የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያበረከቱ መደረጉ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኝ እናቶች የሚወለዱ ህፃናት በወቅቱ የምርመራና ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የማፋጠኛ (accelerated plan) ዕቅድ በማዘጋጀት የተሰሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ዋና ዋና ተግዳሮቶች ከዚህ ቀደም በየደረጃዉ የነበረው የአመራሩ ቁርጠኝነት ዛሬ ላይ መታየት አለመቻል (ለምሳሌ፡- ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ ፕሮግራሞችን በባለቤትነት አለመተግበር)፡፡ በኤችአይቪ መከላከል በጥልቅ የባህሪ ለውጥ ተግባቦት ስራዎች የተደረሱ በተለይም ለኤችአይቪ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች የሚሰሩ ሰራተኞች እና ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ አፍላ እና ወጣት ሴቶች የኤችአይቪ ምርመራ አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የጎላ ክፍተት መኖሩ፤ ተመላክቷል፡፡
የኤችአይቪ ምርመራ አገልግሎት በመንግስትና እና የግል የጤና ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ድረስ በመዝለቅ የተለያዩ የምርመራ ስልቶችን በመተግበር እየተሰጠ የሚገኝ ቢሆንም ቫይረሱ በደማቸው ያለ ሰዎችን ከማግኘት አንፃር የሚጠበቀውን ያህል ውጤታማ መሆን አለመቻሉ፤ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ከሚገኝ እናቶች የተወለዱ ህፃናትን በጊዜው የኤችአይቪ ምርመራ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ክፍተት መኖሩ፤ ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ተከታታይነት ያላቸዉ ፕሮግራሞች ቢተገበሩም ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት የኤችአይቪ መከላከያ መድሃኒት (NVP +AZT Prophylaxis) ዝቅተኛ አፈፃፀም ይኖረዋል፡፡
ዋና ዋና ተግዳሮቶች የኤችአይቪ ፕሮግራም ግብአቶች መቆራረጥ (ለአብነትም የኮንዶም አቅርቦት፤ የኤችአይቪ መመርመሪያ ኪቶች፤ የአባላዘር በሽታዎች ህክምና ኪት) ለኤችአይቪ መከላከል እና መቆጣጣር በተለይም ማህበረሰቡ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ራሳቸውን ይፋ አድርጎ በማስተማር፤ የማይተካ ሚና በመጫወት የበኩላቸውን አስተዋፆ ሲያበረክቱ የቆዩ ቢሆንም ከበቂ ድጋፍ እጦት የተነሳ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ማህበራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከሙ እና እየፈረሱ መምጣት ይጠቀሳል፡፡
የሚዲያ ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎችን የራሳቸው አጀንዳ አደርገው ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠርና ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንፃር ክፍተት መኖሩ፣ በመጀመሪያው 95% እንደ ሀገር የኤችአይቪ በደማቸው ይገኛል ተብሎ ከሚገመቱ ወገኖች መካከል 84 በመቶ የሚሆኑት ተመርምረው ራሳቸውን ያወቁ ሲሆን አሁንም የመጀመሪያ 95% ከማሳካት አንፃር ክፍተት አለ፡፡
በማህበረሰብ ደረጃ መረጃዎችን ለያይተን ስንመለከት ለኤች.አይ.ቪ በይበልጥ ተጋላጭ ሆኖ የሚታዩት የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚከተለዉ ከዚህ በታች በዝርዝር ተመላክቷል
የሴተኛ አዳሪዎች (23 %) አደንዛዥ እፅ በመርፌ የሚወስዱ ሰዎች (14 %) የህግ ታራሚዎች (4.2 %)፤ የትዳር አጋራቸዉ የሞተባቸዉ (11.5 %)፤ ከትዳር አጋራቸዉ ጋር የተለያዩ/የተፋቱ (2.9 %)፤ የረጅም ርቀት መኪና አሽከርካሪዎች (4.9 %)፤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የሚሰሩ ሰራተኞች የአፍላወጣቶች (Adolescents) ሴቶች እና ወጣቶች (Youths) ሴቶች (እድሜያቸዉ ከ15-24) መለዮ ለባሾች (High-risk uniformed ) (1.2 %) ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች የትዳር አጋር በሃገራችን ለኤች.አይ.ቪ ስርጭት መንስዔ ናቸዉ ተብለዉ ከተለይቱ ምክንያቶች ዉስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎች እንደሆኑ ይታመናል፡፡
በማህበረሰቡ ዉስጥ ስለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገድ ያለዉ ግንዛቤ አናሳ መሆን በሃገራችን አጠቃላይ ስለ ኤች.አይ.ቪ መተላለፊያዉ እና መከላከያ መንገድ በማወቅ ደረጃ በወንዶች 39 % ፤ ሲሆን በሴቶች 20 % ነዉ፡፡ (EDHS 2016) በድሬዳዋ አጠቃላይ ስለ ኤች.አይ.ቪ መተላለፊያዉ እና መከላከያ መንገድ በማወቅ ደረጃ በወንዶች 64 % ፤ ሲሆን በሴቶች 45 % ነዉ፡፡ (EDHS 2016)
የሴተኛ አዳሪነት እና ወሲብን በጥቅም የመለወጥ ሁኔታዎች በብዛት መስፋፋት በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ሴተኛ አዳሪ የሚገቡ ታዳጊ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነዉ፡፡ የኤች.አይ.ቪ አገልግሎቶችን የመጠቀም ባህል አናሳ (Low health seeking behavior) መሆን ከአንድ በላይ የወሲብ አጋር በተመሳሳይ ወቅት መያዝ ኮንዶም የመጠቀም ሁኔታ አነስተኛ መሆን 49 % የሚሆኑ ወንዶች በጊዚያዊ ከተዋወቋት ሴት ጋር ያደረጉትን ግንኙነት ኮንዶም አልተጠቀሙም፡፡
ወጣቶች በትንሽ እድሜ ወሲባዊ ግንኙነት መጀመር እድሚያቸዉ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች (በተለይ ሴቶች) የግብረ ስጋ ግንኙነት በእድሜ ከሚበልጣቸዉ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ በጣም እየጨመረ ነዉ፡፡ ጥንቃቄ የጎደለዉ የወሲብ ግንኙነት የሚያደርጉ ወጣቶች ቁጥር መብዛት በዚህም ምክንያት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (post pill) ተጠቃሚዎች ቁጥር መብዛት፤ ውርጃ ሚፈፅሙ ወጣቾች ቁጥር መብዛት፤ እና ያልተፈለግ እርግዝና የሚከሰትባቸዉ ታዳጊ ወጣቶች (teen age pregnancy) ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር እየተስተዋለ ነዉ፡፡
የአባላዘር በሽታ ስርጭት መስፋፋት አልኮል እና አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ መብዛት ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች ህክምናቸዉን በአግባቡ አለመከታተል የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ህክምና በመከታተል ላይ ያሉ ሰዎች በተለያዩ ምክንያት ህክምና እያቋርጡ ነዉ፡፡ የአድሎ እና መገለል ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉን ሰዎችን ማግለልና መድሎ መፈፀም ቫይረሱን ለመቆጣጠር ለሚደረገዉ ጥረት ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ነዉ፡፡
በሃገራችን ላለፉት አመታት ኤች.አይ.ቪን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ የኤች.አይ.ቪ መከላከል (HIV combination prevention) እስትራቴጂን በመከተል ላይ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ሁሉን አቀፍ የኤች.አይ.ቪ መከላከል አገልግሎቶችን በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ይጠቃለላሉ፡፡
- የኤች.አይ.ቪ መከላከል (HIV Prevention Programs)
- ትምህርታዊ ፕሮግራሞች
- የባሃሪ ለዉጥ ፕሮግራሞች (የአቻ ለአቻ፤ የህይወት ክህሎት፤ ወዘተ)
- የኮንዶም አቅርቦትና ስርጭት
- የአልኮል እና ሌሎች ዕፆችን ተጽዕኖአቸውን መቀነስ እና ማስወገድ (Risk reduction)
- የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የሕክምና አገልግሎቶች (Bio-medical services)
- የኤች.አይ.ቪ ምክርና ምርመራ አገልግሎት
- የፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶች ሕክምና አገልግሎት
- ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ/ጽንስ እንዳይተላለፍ ህክምና አገልግሎት
- ከኤች.አይ.ቪ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው በሽታዎች ሕክምና (የቲቢ፤ የአባላዘርና ቫይራል ሄፓታይተስ በሽታዎች ህክምና)
III. መዋቅራዊ ፕሮግራሞች (Structural intervention) ፡-
- ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል አዉንታዊ አስተዋፆ ሊያበረክቱ የሚችሉ አሰራሮችና ህጎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም አሉታዊ አስተዋፆ ያላቸዉን ማስተካኪያ አንዲደረግባቸዉ ማድረግ፡፡
የኤች.አይ.ቪ የምክክርና ምርመራ አገልገሎት (HCT) ዓይነቶች
- በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የኤች.አይ.ቪ ምክክር እና ምርመራ አገልግሎት /VCT/
- በጤና ባለሙያ አነሳሽነት የሚከናወን የኤች.አይ.ቪ ምርመራና ምክክር አገልግሎት (PITC)
- ኤች.አይ.ቪ እራሰን መራስ መመርመር (HIV self-test)
የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ሕክምና አገልግሎት አንድ ሰው ተመርምሮ ኤች.አይ.ቪ በደሙ ውስጥ ከተገኘ በጤና ባለሙያ ትዕዛዝ መሠረት ወዲያውኑ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት ይጀምራል፡፡ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት በጤና ባለሙያ በታዘዘዉ መሰረት በአግባቡ የሚወሰድ ከሆን የሚከተሉት ጥቅሞችን ያገኛል፡-
- የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መጠን እንዲቀንስ (ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በሰዉነት ዉስጥ እንዳይባዛ ይረዳል)
- የሰውነታችን የበሽታ መከላከያ ሲዲ4 መጠን እንዲጨምር ይረዳል
- የተጓዳኝ በሽታዎችን እና ሞትን ለመከላከልና ለመቀነስ ያግዛል
- ጤናማ ሕይወት ለመኖር ያግዛል
- ኤች.አይ.ቪ ወደ ሌላ ሰዉ መተላለፍን ይገታል እንዲሁም ለቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ትልቅ አስተዋፆ ያበረክታል፤
የአድሎና መገለልን ፍራቻ ብዙ ሰዎች የፀረ-ኤች.ኤ.ቪ ህክምና አይከታተሉም፡፡ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት በአግባቡና ሁልጊዜ ከተወሰደ በሰውነት ውስጥ ያለ የቫይረስ መጠን ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይፋ በተደረገው ሳይንሳዊ ግኝት መሠረት የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ህክምና የሚከታተል ታካሚ ጥሩ የመድሃኒት አወሳሰድ ካለዉ፡፡ በደሙ ያለዉ የቫይረስ መጠን ወደ ማይታይበት ደረጃ ይደርሳል፡፡
በዚህም በአንድ ሚሊ ሊትር ደም ውሰጥ ያለው የቫይረስ መጠን ከ50 ከፒ በታች ይወርዳል፡፡ በሰውነት ውስጥ ያለ የቫይረስ መጠን በላቦራቶሪ ምርመራ ወደ ማይታይበት ደረጃ ዝቅ (የማይታይ መጠን ሲደርስ) ጥቅሞቸ ያስገኛል፡፡ ታካሚዉ ለተጓዳኝ በሽታ ያለውን ተጋላጭነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡ ይህ ደግሞ ታካሚዉ ጤናማ እና የዕለት ተዕለት ሥራውን እና ሌሎች ማህበራዊ ክንዋኔዎች ያለችግር መፈፀም ያስችለዋል፡፡
የኤች.አይ.ቪን በግብረ ስጋ ግንኙነት ወደ ትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛዉ የማስተላለፍ እድሉ የተገታ ይሆናል፡፡ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ህክምና ታካሚ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የቫይረስ ልኬት ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እየወሰደ ያለዉ መድሃኒት የቫይረሱን መጠን በምን ያህል እቀነሰ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
የፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒት በመውሰድ ላይ ያለ ታካሚ የሚከተሉትን ማወቅ ይኖርበታል/ይኖርባታል፡፡ በቫይረስ ልኬት ምርመራ ውጤት የቫይረሱ መጠን አይታይም ማለት ቫይረሱ ጠፍቷል፤ ወይም ታካሚዉ ከኤች.አይ.ቪ ነፃ ነው ማለት አይደለም፡፡ የቫይረሱን በማይታይበት ደረጃ ለማስቀጠል ታካሚዉ ጠንካራ የመድሀኒት ቁርኝት ሊኖረዉ ይገባል፡፡
በተገኘው የቫይረስ ልኬት ምርመራ ውጤት በመርካት ወይም በሌላ ምክንያት የሚከታተለዉን መድሃኒት መዉሰድ ከተወ በሰውነት ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን መልሶ እንዲጨምርና ላልተፈለጉ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድል ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡
ዝቅተኛ የቫይረስ ልኬት ምርመራ ውጤት ወደማይታይ ደረጃ ሁሌም እንዲሆ መድሃኒቱን ሁል ጎዜ በአግባቡ መዉሰድ እና ወቅቱን ጠብቆ የቫይረስ ልኬት ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የማይታይ የቫይረስ መጠን የደረሰ ታካሚ የኤች.አይ.ቪ መከላከል ጥንቃቄዎችን (ታማኝ መሆን ወይም ኮንዶመ መጠቀም ) ማድረግ አለበት፡፡
ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የመከላከል ፕሮግራም (Pmtct) ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እናቶች የቅድመ ወሊድ አገልግሎት፣ የወሊድ አገልግሎት እና የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒትን በአግባቡ መከታተል እንዲሁም ጡት በማጥባት ወቅት የጤና ባለሞያ ምክር በመከተል እና ተያያዥ የህክምና አገልግሎቶችን በመጠቀም ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ልጅ ወልዶ ማሳደግ ይቻላል፡፡
ከሌላዉ ፕሮግራሙ አፈፃፀም አናሳ መሆን የሚጠቀሰዉ ምክንያት የባሎች ተሳትፎ አናሳ መሆኑ ነዉ፡፡ በ2014 ዓ.ም ምርመራ ከመጡ ነፍስጡር እናቶች የትዳር አጋራቸዉ አብሯቸዉ ለምርመራ ወደ ጤና ተቋም የመጡ ባሎች 24% ብቻ ናቸዉ፡፡ ከኤች.አይ.ቪ ነፃ ትዉልድ ለማፍራት የባሎችም ተሳትፎ ትልቅ አስተዋፆ አለዉ፡፡
የአባላዘር በሽታ ምርመራ እና ህክምና አገልግሎት የአባለዘር በሽታ ምልክቶች በታየ ጊዜ በወቅቱ ምርመራ በማድረግ ህክምና ካልተደረገ በኤች.አይ.ቪ የመያዝን እድል በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡ የአባላዘር በሽታ ምልክንያቶች በታየ ጊዜ በአፋጣኝ እራሶን እና ፍቅረኛዎትን/የትዳር አጋሮን/የወሲብ ተጓዳኞት ህክምና ማስጀመር አለቦት፡፡ በ2014 ዓ.ም ለዓባላዘር ህክምና ወደ ጤና ተቋም መጥቶ ህክምና መዉስድ ካለባቸዉ ሰዎች 43% ያህል ብቻ ነዉ ህምናዉን የወሰዱት፡፡
የአባላዘር ህክምና ሽፋን በሚፈለገዉ መጠን ከፍ እንዳይል ከሚያደርገዉ ምክንያቶች አንዱ እና ዋነኛዉ በማህበረሰባችን ዉስጥ ስለ አባላዘር በሽታ ያለዉ የተሳሳተ አመለካከት ነዉ፡፡ በማህበረሰባችን ዉስጥ ያለዉን የተሳሳተ አመለካከት በማስተካከል የበሽታዉ ምልክት የታየባቸዉ ሰዎች ከልማዳዊ አመለካከት ይልቅ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምናዉን በመከታተል መዳን እንደሚቻል በማሳወቅ የአገልግሎት ተጠቃሚዎችን ማሳደግ ይጠበቃል፡፡
አጠቃላይ ማህበረሰቡ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ አገልግሎቶች ተደራሽነታቸዉን መረጋገጥ (በተለይ ለይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች) ወጣቶችን (በት/ቤት እና ከት/ቤት ዉጭ ያሉ) ለኤች.አይ.ቪ አጋላጭ ከሆኑ ባሃሪ እንዲታቀቡ እና አዉንታዊ ባህሪ እንዲያዳብሩ ማገዝ አድሎ እና መገለልን ማስቀረት (በማህበራዊ ህይወት፤ በስራ ቦታ፤ ወዘተ) ኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ያለባቸዉ ወገኖች አስፈላጊዉን እገዛ ማድረግ ይገባል፡፡
በየደረጃዉ ያለ አመራር ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት መንስዔዉ ዘርፈብዙ እንደመሆኑ እና የሚያስከትለዉም ተፅዕኖ ብዙ ከመሆኑ አንፃር፤ ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገዉ ጥረትም ዘርፈ ብዙ መሆን ይኖርበታል፡፡ በየደረጃዉ ያለ አመራርም ህን ከግንዛቤ በማስገባት ለዘርፍ ብዙ ኤች.አይ.ቪ ምላሽ አስፈላጊዉን ትኩረት መስጠት፤ በቂ በጀት መመደብ እና የፕሮግራሞችን ተፈፃሚነት ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
የሲቪክ ማህበራት ለኤች.አይ.ቪ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ትኩረት በመስጠት የኤች.አይ.ቪ ፕሮግራሞችን ተደራሽ ማድረግ፡፡ የአድሎ እና መገለልን ለማስቀረት ማህበረሰቡን ማስተማር ወጣቶች ከኤች.አይ.ቪ እራሳቸዉን እንዲከላከሉ ማብቃት እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ አገልግሎቶችን ለሁሉም የህበረተሰብ ክፍል ያለምንም አድሎ መስጠት ለኤች.አይ.ቪ ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ትኩረት አድርጎ የመከላከል አገልግሎት መስጠት የኤች.አይ.ቪ/ኤደስ ስርጭትን ለመከላከል ከእኔስ ምን ይጠበቃል? ብሎ መነሳት ያስፈልጋል፡፡


