የልኡካን ቡድኑ አባላት ድሬዳዋ አስተዳደር ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ባዩ እና የአስተዳደሩ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ልኡካን በድሬዳዋ አስተዳደር በሚኖረው የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት በአስተዳደሩ የተከናወኑ የልማት ስራዎች በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርግ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል ፡፡
በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፌ ኑርሰን የሚመራው የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አባላት ልኡክ በድሬዳዋ አስተዳደር ቆይታው የፊፋን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በማሟላቱ የማረጋገጫ ሰርተፊኬት የተሰጠውን የድሬዳዋ አለማቀፍ ስቴዲየምን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ፤በተለያዩ ተቋማትና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ያሉ ልምዶች ልውውጥ ይደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
በዳንኤል አማረ
ፎቶ አብይ ሽመልስ


