መድረኩን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዲሁም ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ በጋራ የመሩት ሲሆን የዘጠኝ ወር የመንግስታዊ እቅድ አፈጻጸም በሪፖርት ግምገማ መድረኩም በዋናዋና ቁልፍ ተግባራት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ የማስፈፀም አቅም በሀብት አጠቃቅም እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ከመድረኩ ጋር በተያያዘ ያሉትን ዝርዝር መረጃዎች የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።


