በድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ስርዓቱን የተሳለጠ ለማድረግ እና በኢኮኖሚው ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስመጪዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፍስሃ ይታገሱ ገለፀ።
በሀገራችን በንግድ ስርዓቱን የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮች በመከሰታቸው በምርት አቅርቦት ላይ ችግር እየተከሰተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አስመጪዎች በበኩላቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ቅንጅት አለመኖሩ ችግሮቹ በስፋት መከሰታቸውን ጠቁመው ከግምሩክ ስርዓት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች በመኖራቸው ለህብረተሰቡ በፍትሃዊ መንገድ የፋብሪካ ምርቶችን ለማቅረብ አዳጋች እንደሆነባቸው ጠቁመዋል።
በገበያው ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስመጪዎች ምርትን በፍራንኮቫሉታ ቢፈቀድም በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ምርቶችን ለማስገባትና ለነጋዴው ለማስረከብ አዳጋች እንደሆነባቸው ገልፀዋል።
በምርት ጥራትና ፍተሻ ላብራቶሪ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚታይ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ አስመጪዎቹ ጠቁመዋል ።
የንግድ ስርዓቱን የሚያባብሱ ችግሮችን በመለየት በቀጣይ ለመፍታት መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይም ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር እንደጠቆሙት በአለም አቀፍ ደረጃ በመሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ልዩነት በመፈጠሩ በተወሰኑ ምርቶች ላይ መጠነኛ ጭማሪ መከሰታቸውን ገልፀዋል።
ከምርት ፍተሻና የላብራቶሪ አገልግሎት ለማረጋገጥ አዲስ አበባ ድረስ በመላክም የትራንስፓርት እና ከግዜ ጋር በተያያዘ ችግር እንደሆነባቸው ጠቁመዋል።
መንግስት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እና በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጠረውን ሰው ሰራሽ ዋጋን ለመቆጣጠር በፍራንኮቫሉታ እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው አስመጪዎችን በርካታ የፋብሪካ ምርቶችን ለአስተዳደሩ እና ለክልል ከተሞች በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፋብሪካ ምርት አቅራቢዎች ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት በቀጣይ ለመፍታት እንደሚሰራ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፍስሃ ይታገሱ አሳስበዋል።


