የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ወረዳዎች እና የገጠር ክላስተሮች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ተገመገመ

የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2016 በጀት አመት የ 9 ወር የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ፣ የከተማ ወረዳዎች እና የገጠር ክላስተሮች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በዛሬ እለት የተጀመረ ሲሆን በከሰዓቱ ውሎም የዘጠኙ የከተማ ወረዳዎች እና የአራቱ የገጠር ክላስተሮች የ 2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገምግሟል ።

የሪፖርት ግምገማ መድረኩን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የመሩ ሲሆን በመድረኩም የከተማ ወረዳዎች እና የገጠር ክላስተሮች በስድስት ወራቶች ውስጥ በልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ የሰሩአቸው ስራዎችም አቅርበዋል። የቀረቡትን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግም ከመድረኩ ሀሳብ እና አስተያየት ተሰቶበት ሰፊ ውይይትም ተደርጓል ።

በመጨረሻም የቀበሌ ቤቶች ላይ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት መኖር እንደሚገባው ፣ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተናቦ መስራቱ ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፣ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት ፣ ህገ-ወጥ ንግድን መከላከል እንደሚገባ እንዲሁም ፅዳት እና ውበት ላይም ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባም ነው የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በማጠቃለያው ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡት ።

በሪፖርቱ ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በቀጣይ ሰፊ ትኩረት ተደርጎበት እንዲሰራ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ ተናግረዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *