በመድረኩም የአስተዳደሩ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ሀይለማሪያም ዳዲ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
በአስተዳደሩ ገቢን በተመለከተ በባለፋት ዘጠኝ ወራት ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን ይህም የእቅዱን 85%ማሳካት መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በአጠቃላይ በአስተዳደሩ ከሚሰበሰበው እና ከፌደራል ከሚገኝው ድጎማ ተጣምሮ ከሚገኝው 7.1ቢሊዮን ብር ውስጥ በባለፋት ዘጠኝ ወራት 5.1 ለመሰብሰብ ታቅዶ 4.1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ እና በዚህም የእቅዱን 95 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።
የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን በተመለከተ የመስኖ ሰብሎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት 2,830 ሄክታር መሬት በልማት ለመሸፈን ታቅዶ 2,717 በማልማት የእቅዱን 95% ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።
በሰብል እና ሆርቲካልቸር ልማት ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ በባለፉት ዘጠኝ ወራት 6,500 አርሶ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 6,303 ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የእቅዱን 97 በመቶ ማሳካቱን በሪፖርቱ ተገልጿል።
በስራ እድል ፈጠራ፣በመሰረተ ልማት አገልግሎት፣በማህበራዊ በትምህርት በጤና እና በልዩልዩ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ እና በቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንድስትሪእና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ሀርቢ ቡህ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰው በተለያየ ምክንያት ዝቅተኛ እቅድ አፈጻጸም ያላቸውን ተግባራትን በማካካሻ ዕቅድ በመከለስ ዓመታዊ ዕቅዱን ግብ ማስመታት እንደሚገባ አስምረውበታል፡፡ ሥራዎችን በለውጥ ትጋት ለማከናወንና የስኬት ከፍታ ለመጨመር የጋራ መግባባት በመፍጠር ግምገማው ተጠናቋል።


