የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የመሰረተ ልማት ገንቢ ተቋማት በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ::

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም እሳት አደጋ በድንገት የሚከሰት እና ለበርካታ ንብረት መውደም ምክንያት የሚሆን አደጋ መሆኑን ገልፀው ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ ከተማ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ለበርካታ ንብረት መውደም ምክንያት እንደነበርና ነገር ግን እሳት አደጋው ሲከሰት እሳቱን ለማጥፋት መስዋዕት የሚከፍሉ የእሳት አደጋ ባለሞያዎች እና የስራ ሀላፊዎች ምስጋናቸውን እንደሚገባቸው ኢንጂነር ጀማል ተናግረዋል ።

የድሬዳዋ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት እሳቱ በሰው እንዲሁም በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በአፋጣኝ እሳቱን ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ከዚህ ባለፈም የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ከድሬዳዋ በዘለለ ለአጎራባች ክልሎችም በበቂ ሁኔታ ማገልገል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማሻሽያ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሰሙ ታከለ በእለቱ ተናግረዋል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- በአብይ ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *