በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ ስራዎች በስፋት እንደሚሰሩ ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በዛሬው ዕለት አካሄደ ።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አስተዳደራችን ካለው መልካ ምድራዊ አቀማመጥ አንፃር ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ በመሆኑ የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩን ህይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባራትን በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖን መቋቋም የሚችል አቅም በመገንባት አማራጭ የገቢ ምንጭ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል::

ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አያይዘውም ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናወን የፕሮጀክቱ ዋነኛ አላማ አድርገን መስራት ይገባናል ያሉ ሲሆን ፕሮጀክቱ በቀጣይ አምስት አመታት እንደሚተገበርም ተናግረዋል::

በመጨረሻም ለፕሮጀክቱ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ በተሳካ ሁኔታ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል::

የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማእድን ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ 4 የገጠር ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑን ገልፀዋል::

አቶ ኑረዲን አያይዘውም በዚህ ፕሮጀክት አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩ ያለ

በትን ዘርፍ ብዙና ውስብስብ የልማት ጥያቄዎችን በመቅረፍ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ እየጨመረ የመጣውን የአደጋ ስጋት በመቀነስ ከድህነት የመውጣት ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል::

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ ከ13 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዶላር በላይ በጀት በአለም ባንክ አማካኝነት እንደተመደበለትም ከመድረኩ ተገልጿል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *