የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ ታደርጋለች- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ እንደምታደርግ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽሥላሴ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በዲፕሎማሲው ረገድ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ በደረሰችው ስምምነት አማራጭ ወደብ እና የባህር በር ማግኘት መቻሏን አስታውሰዋል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ “የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ትኩሳት ለማርገብ እና ገጽታዋን ለማጠልሸት…


