ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጉብኝተዋል፦ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

በሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባለፈው በጀት ዓመት የአገልግሎቱ ዘርፍ 7 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

በአገልግሎት ዘርፍ የሚመደበው ቱሪዝም የብዝኃ ዕድገት አመራር አንዱ ቁልፍ ዘርፍ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንት ታዬ በዚህም መሰረት ከአንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ በላይ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በተከናወኑ የገበታ ለሀገር የቱሪዝም መዳረሻ ኢኒሼቲቮች አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋፋት እና ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማሻሻል መቻሉን አንስተዋል።

እንደ ገበታ ለሀገር ሁሉ በገበታ ለትውልድም አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች እየለሙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

.EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *