የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የዲጂታል መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልጸዋል።
እስከሁንም በረካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የህግ እና የፖሊሲ ማእቀፎች ወደስራ ገብተዋል ብለዋል።
የመንግሥት አግልግሎቶችን ጥራት እና ተደራሽነት በማሳደግ 737 የመንግሥት አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ለዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ከዚህ ባለፈ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት አስፈላጊ እንደሆነ በማመን የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮጀከት ይፋ መደረጉን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።
በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች እና የመንግሥት ሰራተኞችን ክህሎት የማበልጽግ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
EBC


