የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ ታደርጋለች- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ እንደምታደርግ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዲፕሎማሲው ረገድ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ በደረሰችው ስምምነት አማራጭ ወደብ እና የባህር በር ማግኘት መቻሏን አስታውሰዋል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎ “የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ትኩሳት ለማርገብ እና ገጽታዋን ለማጠልሸት የሚካሄደውን ዘመቻ ለማክሸፍ” በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

በቀጣናው የሀገሪቱን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉልህ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን በተለይ የሱዳን ግጭት እንዲፈታ እያደረገችው ያለው “ግልጽ እና ተከታታይነት ያለው የሰላም ዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል“ ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗ የኢትዮጵያን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኀበራዊ ትሩፋቶች ለማሳደግ እና ሚዛናዊ ግንኙነትን ይበልጥ ለማዳበር ዕድል እንደሚፈጥርም አብራርተዋል፡፡

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *