አሰናካይ ሐሳቦችን በማረቅ ወደ ፊት መራመድ አስፈላጊ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጥልቅ ማስተዋል፣ ማሰላሰል፣ አርቆ ማሰብ እና ትዕግስት የኢትዮጵያ የጽናት ዋልታዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሊታረሙ እና ሊታረቁ በሚችሉ የፖለቲካ ልዩነቶች ሳቢያ ለድህነት እና ለሌሎች ሀገራዊ ችግሮች ስትዳረግ መቆየቷንም አንስተዋል፡፡
በየዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት መንግሥት ዘርፈ ብዙ የዕድገት አማራጮችን ነድፎ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ጭምር ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሏ ሀገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ የያዘችው ውጥን እየሰመረ መምጣቱን እንደሚያሳይ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት 8.1 በመቶ ጥቅል ሀገራዊ የኢኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሏ ፈተናዎችን የሚሻገር ሥርዓተ አኮኖሚ እየተገነባ መሆኑን እንደሚያሳይም ተናግረዋል፡፡


