የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ለመቀነስ እንዲቻል በዛሬው እለት የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄዱ::

በመርሀ-ግብሩ ላይ ደም ሲለግሱ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች በተለያዩ ጊዜያት የሚለገሰው ደም በየሆስፒታሉ በወሊድና በተለያዩ ምክንያቶች ደም በማጣት የሚሰቃዩ ወገኖችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናገረው፤ ደም መለገስ የውስጥ እርካታን እንደሚፈጥርና ሰብአዊነት ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም በቀጣይም በዚህ መልኩ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ደም መለገሳቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *