በድሬዳዋ አስተዳደር “የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሁለተኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቅቋል።
የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶም ሀሳባቸውን ለድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ያካፈሉ ሰልጣኝ አመራሮች በተጨባጭ ሀገራችንን ለማሳደግና የብልፅግና ጉዟችንን ለማሳካት ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳላው በመግለፅ በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችንንም አጠናክረን ለማስቀጠል እና ላለፉት ተከታታይ አስር የስልጠና ቀናት በፅንሰ ሀሳብና በነባራዊ ሁኔት የተደገፈ እውቀት ማግኘታቸውን አንስተው ስልጠናውን በመረጃ በተደገፈ መልኩ መከታተላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሰልጣኞቹ በተለይ የሀገራችንን እድገት ለማፋጠን ህልማችንን ተከትለን በቁርጠኝነት መስራት እጅግ አስፈላጊ ስለመሆኑንም ከስልጠናው ተገንዝበናል ሲሉ ተናግረዋል::
አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም ብልፅግና ፓርቲ በየጊዜው አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት የአቅም ግንባታ ላይ አትኩሮ እየሰራ መሆኑ የአመራሩን እውቀት የሚያሰፋ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ነው ሲሉ ጠቁመዋል::
በቀጣይ ከስልጠናው ያገኘነውን እውቀት ወደ መሬት በማውረድ ማህበረሰባችንን እና ሀገራችንን በይበልጥ ከፍ ባለ ደረጃ በማገልገል የብልፅግና ጉዞአችንን አናፋጥናለን ሲሉም ተናግረዋል::
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


