ሀብትን ማሳወቅና ማስመዝገብ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተገለፀ
የድሬዳዋ አስተዳደረ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአስተዳደሩ ለተውጣጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ለጤና ተቋማት ሀላፊዎች እንዲሁም ለሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ሀላፊዎች በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀመረ:: በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር የስልጠና መድረኩ ዋነኛ አላማ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ፅንሰ ሀሳብና አተገባበር ላይ ግንዛቤ…


