ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚኒስትሮች ምክር ቤትን የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በመሰብሰብ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀምረዋል።

ግምገማው ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዝንባሌዎችንና ፍኖቶችን በመፈተሽ በኢትዮጵያ ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ተመልክቷል።

8.45 በመቶ በተተነበየው የመጪው ዓመት እድገት የለውጡ አበረታች ውጤቶች አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያሳዩ፣ የጨመረ የመንግሥት ገቢ እና ኢንቨስትመንት ያስገኙ፣ የመንግሥት ዕዳን የቀነሱ፣ በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትን ተወዳዳሪነት የጨመሩ፣ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙ፣ የበለጠ ተወዳዳሪነትን የታየበት የፋይናንስ ዘርፍ ያመጡ፣ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን የፈጠሩ ብሎም የዘርፍ ምርታማነትን ያሳደጉ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በተለይም እንደ ማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን ባሉ ዘርፎች የተፋጠነ እንደሚሆን ይጠበቃልም መባሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

EBc

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *