#ዜና “የዛሬ ተመራቂዎች ከስልጠናው ካገኛችሁት እውቀት በተጨማሪ ራሳችሁን በቴክኖሎጂ በማሳደግ ማህበረሰቡን ማገልገል ይጠበቅባቹሀል”

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ በመሆን በተለያዩ መስኮች ያሰለጠኗቸውን 681 ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመርቀዋል::

በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመገኘት ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ በሰልጠና ቆይታችሁ ካገኛችሁት እውቀት በተጨማሪ በየጊዜ እራሳችሁን በቴክኖሎጂዎች በማበልፀግ ተመረራጭ ለመሆን ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቹሀል ሲሉ ተናግረዋል::

በአሁኑ ሰአት ነፃ የንግድ ቀጠናን ጨምሮ በድሬዳዋ በርካታ የኢንደስትሪ ተቋማት እየተስፋፉ መሆኑን ከንቲባ ከድር ጠቅሰው ይሄም ኢኮኖሚውን ከማሳደግ በተጨማሪ የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

በመጨረሻም ክቡር ከንቲባ ከድር ለተመራቂዎች መልካም የስራ ጊዜን በመመኘት ማህበረሰቡን በትጋት ማገልገል እንደሚገባ ጠቁመዋል:

የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው በዛሬው እለት በአጠቃላይ በተለያዩ መስኮች 681 ሰልጣኞች እንደተመረቁና 447 ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል::

በአስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማሻሻልና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የጠቆሙት አቶ ሮቤል ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል::

ተመራቂዎች በበኩላቸው በሰለጠንበት የሙያ መስክ በታማኝነትና በቅንነት ማህበረሰባችንን ለማገልገል ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *