” በጎነት ለኢትዮጲያ ከፍታ ” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ 2016 የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ ማጠቃለያ መርሀ-ግብር በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በዛሬው እለት ተካሂዷል ።
ባሳለፍነው አመት የክረምት ወራት የበጎ-ፍቃድ አገልግሎት በ 14 የተለያዩ መርሀ ግብሮች መከናወኑ ይታወቃል ። ከነዚህም 14 መርሀ-ግብሮች ውስጥም እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ሁሉንም መርሀ-ግብሮች ከማከናወን በዘለለ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ የሚሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን የራሳቸውን ሶፍትዌር በማልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ በመውጣት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፕላቲኒየም ተሸላሚም ሆኗል ።
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በተካሄደው የማጠቃለያ መርሀ-ግብር ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የወጣቶች በጎ ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ባሃር አብደላ በመገኘት ለአስተዳደሩ የተበረከቱትን የተለያዩ ሽልማቶችን መቀበልም ችለዋል ።


