ሀብትን ማሳወቅና ማስመዝገብ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደረ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአስተዳደሩ ለተውጣጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ለጤና ተቋማት ሀላፊዎች እንዲሁም ለሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ሀላፊዎች በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀመረ::

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር የስልጠና መድረኩ ዋነኛ አላማ በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ፅንሰ ሀሳብና አተገባበር ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ጠቁመዋል::

ሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት አቶ ፌኑስ ስለ ሀብት ምዝገባና ጠቀሜታም ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል::

በመጨረሻም አቶ ፌኑስ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛና አመራር ሀብቱን በማስመዝገብና በማሳወቅ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *