በስነ-ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማ ለሚገኙ 1 ኛ እና 2 ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ም\ርዕሰ መምህራን ፣ ወተመ ፣ የግብረገብ ፀረ-ሙስና እና ሪከርድና ማህደር በተማሪዎች ሥነ-ምግባር ላይ የድጋፍ ሰጪዎች ሚና እንዲሁም በሥነ-ምግባለሙያዎችባር እና ሙስና ምንነት ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና በዛሬው እለት ተሰቷል ።

በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ የአንድ ሀገር መሰረት የሆነው ትምህርት እንደመሆኑ መጠን በስነ-ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ብቁ በማድረግ ሀገራቸውን የሚያገለግሉ እና የሚያስጠሩ ይሆኑ ዘንድም መስራት እንደሚገባ ተናግረው የድሬዳዋ ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንም እየሰራቸው ላለው በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሁሉ አቶ አቡበከር በእለቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ተማሪዎች ከምንም በላይ እራሳቸውን በስነ-ምግባር በማነፅና ውጤታማ በመሆን የሀገራችንን እድገት እና ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ሁሉ የራሳቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ፌኑስ አብዱልጀባር ገልፀው ለዚህም መሳካት መምህራን ፣ ወላጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ነው አቶ ፌኑስ ያስታወቁት ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *