የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እና ተጠሪ ተቆማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ ።
በድሬዳዋ አስተዳደር የሴፍትኔት ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎችን ማህበራዊ የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ በአግባቡ እያጣራን ፍታዊነትን ለማረጋገጥ ስራ መጀመሩን የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ተናግረዋል ።
በከተማ ስራአስኪያጅ ፅፈትቤት ስር የተጀመሩትን የሶስተኛው ትውልድ ሪፎርም ስራ በተቀመጠለት ቀነ ገደብ እንዲጠናቀቅ የተጀመረው ስራ በአግባቡ መገምገሙን ተናግሯል ።
የሰራተኛውን የስራ ምችችት እና የብቃት ማሻሻል እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ለመከተል የተጀመረው ጥረት ላይ በግምገማ መድረኩ የተሳተፉት ባለሞያዎች እና አመራሮች ለጋራ እድገት ጥረት እንዲያደርጉ ይጠበቃል ሲሉ የፅህፈት ቤት ሃላፊ ተናግረዋል ።
የከተማ ስራስኪያጅ ፅፈትቤት የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ፀደይ በቀለ በሩብ አመቱ የማዘጋጃቤታዊ ገቢ ማሳደግ እና የከተማውን ነዋሪዎች ጥያቄዎች የሚፈቱ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ የሰራተኛውን ቁረጠኝነት የሚጨምር የግምገማ መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል ።
አንደ ከተማ ስራአስኪያጅ ፅፈትቤት የበጀት እጥረት ፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት ችግር እና የማዘጋጃቤታዊ ገቢ ማነስ እንደችግር 2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሩብ አመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የታየ ችግር መሆኑን ዳሬክቶሬት ዳሬክተሯ ጠቁመዋል ።
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅፈት ቤት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞች በቀጣይ የታዩ ድክመቶችን በማሻሻል ላጋጠሙ ችግሮች የተሻለ መፍትሔ ለመፍጠር በጋራ የተግባባንበት መድረክ ነው ብለዋል ።


