#DGC ጥቅምት 14/2017
የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 በጀት አመት የ 1 ኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር ተቋማት ፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በከሰዓቱ መርሀ-ግብር የከተማ ወረዳዎችና የገጠር ክላስተሮች የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል::
በዚህም በቀረበው ሪፖርት ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አማካኝነት ግምገማና ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል::
ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ማህበረሰቡን በተቀላጠፈ መልኩ ለማገለገል እንዲሁም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ ይህ የግምገማ መድረክ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናገረዋል::
ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አያይዘውም በሩብ አመቱ የታዩ አንዳንድ ክፍተቶች ላይ ተተኩሮ እንደሚሰራም አመላክተዋል::
በመድረኩ ማጠቃለያም በወረዳዎች የተጀመሩት አገልግሎትን ዘመናዊና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ የማዘጋጃ ቤት ገቢን መጨመር ላይ በቅንጅትና በርብርብ እንዲሰራ፣ የነዳጅ የቁጥጥር ስርአት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው፣ ወረዳዎች ከእናት መስሪያ ቤት ጋር ተናበው እንዲሰሩ፣ የቅዳሜንና የእሁድ ገበያን ማጠናከር እንደሚገባ፣ ባዶ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ የማስገባት ስራዎች መሰራት እንደሚገባቸው፣ ቅሬታዎች ሲፈጠሩ በተቀላጠፈ መልኩ እንዲፈቱ፣ ከከተማ ፅዳትና ደንብ ማሰከበር ጋር ተያይዞ ተተኩሮ እንዲሰራ፣ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ፣ የወጣት የስእብና ማእከላትን ማጠናከር እንደሚገባ፣ እንዲሁም የቀበሌ ቤቶችን በአግባቡ ማስተዳደር ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጠዋል::
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


