ብቃት ያለው ጠንካራ አደረጃጀት እንዲፈጠር ጠንካራ መሪ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ የሩብ አመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀምን እንዲሁም የአመራር ሽግሽግንና በአደረጃጀት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል::

በዚህም የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅፈት ቤት በ2016 በአደረጃጀት በዘርፍፉ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ አቶ ደረጀ ገልፀው በተለይም አደረጃጀትን መልሶ የማደራጀትና የማጥራት ስራዎች በዝግጅት ምእራፍ እንደተከናወኑና በአጠቃላይ 315 የሚደርሱ መሰረታዊ ድርጅቶች መፈተሻቸውን ተናግረዋል::

በተጨማሪም በመመሪያዎች፣ በፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱንም ጨምረው ገልፀዋል::

በተግባር ምእራፍ ስራዎችም ፓርቲውን በጠንካራ አባላት የማጠናከር ስራ መሰራቱን አቶ ደረጀ ገልፀው የአባላት ምልመላ እንደተደረገና ከዚህም ባሻገር ግንባር ቀደሞች እንደተለዩና 359 ተተኪ አመራሮችን በመለየት የማዘጋጀት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል::

የፓርቲው መመሪያ በሚያዘው መሰረትም የስነ ምግባር ጉድለት የታየባቸውን እና ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱ የተገለፀ ሲሆን 6 አመራሮች ከሃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን በ 39 አመራሮች ላይ ሽግሽግ መደረጉን አቶ ደረጀ ጠቁመው በመሠረታዊ ድርጅትና ከህዋስ 470 እንዲሁም በክብር የተሸኙ 3 አመራሮች መሆናቸው ገልፀዋል ።

ጠንካራ የፋይናንስ ስርአት መዘርጋቱንም ያነሱት አቶ ደረጀ ስርአቱ ግልፅና መመሪያን የተከተለ መሆኑን አመላክተዋል::

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *