የድሬዳዋ አስተዳደር አስተማማኝ ሰላሟን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፀጥታና ደህንነት ዘርፍ ዙሪያ ለስትራቴጂክ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ ስልጠና በዛሬው እለት መሰጠት ተጀመሯል ።

በመርሀ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ፖሊስ ለውጡን ማራመድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለአመራሩና አባላቱ የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ክፍተቶችን የመሙላት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ተናግረው ስልጠናው በተለይም የምስራቅ አጎራባች ክልል ፖሊሶች እና ባለድርሻ አካላት የፀጥታ ስራዎችን አብሮ ከመስራት ባሻገር በጋራ በመሰልጠን ለምስራቁ የሐገራችን ፀጥታ ስራ የጋራ ግንዛቤ የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል ።

ለነዋሪው ህብረተሰብ ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት የሚቻለው ከዚህ ቀደም ሲሰራባቸው በነበሩት ሂደቶች ሳይሆን በተለወጠ መንገድ መሆን ስላለበትና ይህንንም ለማድረግ ስልጠና በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮምሽነር አለሙ መግራ ተናግረው አሁን ላይ በድሬዳዋ በቀንም ሆነ በምሽት አስተማማኝ የሆነ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

በዚሁ ስልጠና የፌደራል ፖሊስ ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ፣ የሐረሪ ፖሊስ ፣ የምስራቅ ሐረርጌ ፖሊስ እንዲሁም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የድሬዳዋ አስተዳደር ማረሚያ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ስልጠናውም ዛሬ እና ነገ የሚካሄድም ይሆናል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *