በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ህጻናት የትምህርትና ማህበራዊ ግንኑኙነት እድል እንዲያገኙ ማስቻል እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ

#DGC ህዳር 22/2017

ለታሪክ የኦቲዝም ማዕከል በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ አስር የሚሆኑ ህጻናትን የመዋያና የመመሪያ ማዕከል ስራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ኦቲዝም በጥቅሉ ከአዕምሮ እድገት ውስንነት ጋር ተያይዞ የሚከሰት እንደሆነ የሚገለፅ ሲሆን በማህበረሰቡ ዘንድ ችግሩን በተመለከተ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዳለ ይታያል፡፡በድሬደዋ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ህፃናትን የጤና ፤ የትምህርት በአጠቃላይ በማህበራዊ ህይወት የእለት ከእለት ግንኙነት እኒዲያዳብሩ ከማስቻል አንፃር በጉዳዩ ላይ የሚሰራ ማእከል አልነበረም፡፡

ይህንን ሁኔታ የተመለከቱትና በኦቲዝም ጥላ ስራ ያለ ልጅ እናት የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት በቀለ በድሬደዋ የኦቲዝም ማዕከል ለማቋቋም ያስባሉ እናብ በብዙ ጥረት የለታሪክ የኦቲዝም ማዕከል በመመስረት ወደስራ ይገባሉ፤ ይሁን እንጂ ማዕከሉን በሚገባ ተንቀሳቅሶ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ህፃናትን በሰፊው ተደራሽ ለማድረግ ውጣውረዱ እጅግ ከፍተኛ በተለይም የበጀት ችግር ፈታኝ እንደሆነ የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪሃጅ ወ/ሮ ሰናይት ይገልፃሉ፡፡

በኦቲዝም የተጠቁ ህፃነት ተገቢውን ትኩረት ካገኙ ወደ ፊት የራሳቸውን ህይወት መምራት የሚችሉና ለአገር የሚጠቅሙ ዜጋ መሆን የሚገልፁት ወ/ሮ ሰናይት ህፃናቱ እራሳቸውን እንዲችሉ በመደገፍ እረገድ ህብረተሰቡም ሆነ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው ጥሪ አቅረበዋል።

ማእከሉ አሁን ላይ ከተላያዩ አካላት የግብአትና ሌሎች ድጋፎችን በመጠየቅ እየሰራ እንደሚገኝ አሁንላይም ከትምህርት ቢሮ ባገኝው ድጋፍ ለገሃር ጋር የሚገኝ ቀደም ሲል የህዝ ቤተመፅሃፍት የነበረ አሁን አገልግሎት ያቆመ ቦታ በመረከብ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ አስር የሚሆኑ ህጻናትን የመዋያና የመመሪያ ማዕከል ስራ ለማስጀመር ከድሬደዋ ሲቪል ሶሳይቲ ኔትዎርክ ጋር በመተባበር እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩ ገልፀዋል፡፡

የድሬደዋ ሲቪል ሶሳይቲ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ አበራ ለታሪክ የኦቲዝም ማዕከል በዚህ ችግር ውስጥ ጣሉ ህፃናትን ተደራሽ ለማድረግ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ማዕከሉን በቀጣይም በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍ ጥረት እንሚደረግ ተናግረዋል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *