በሶማሊያ የግዛት አንድነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ጥያቄ የለውም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በሶማሊያ የግዛት አንድነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ጥያቄም ይሁን ብዥታ የለውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዲፕሎማሲን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ “የሶማሊያ ህዝብ ጎረቤት ብቻ ሳይሆን ወንድምና እህት ህዝብ ነው፤ ለሶማሊያ ሰላምና አንድነት ሞተናል” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ግዛት አንድነት ከየትኛውም ሀገር በላይ ከፍተኛ…


