የኮሪደር ልማት በዋናነት የዋና ዋና መንገዶች አካባቢን የማልማት እንዲሁም ፅዱና ውብ የማድረግ ስራ የሚሰራበት ፕሮጀክት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ
በድሬደዋ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዓላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ከወረዳ 02፣ ከ03 እና 04 ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬደዋን ብልፅግናና ዘመናዊ ከተማነት በላቀ መልኩ ለማስቀጠል በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የኮሪደር ልማት በዋናነት የዋና ዋና መንገዶች አካባቢን ማልማት እንዲሁም ፅዱና ውብ የማድረግ ስራ የሚሰራበት…


