የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሰኞ ነሀሴ 6/2016 እስከ ነሀሴ 12/2016 ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር የምክክር እንዲሁም የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሚያካሄድ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ የኢትዮጲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከፊታችን ሰኞ አንስቶ በሚካሄደው የምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ላይም የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ፣ በከተማ አስተዳደሩ ላይ የሚገኙ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች ፣ የተለያዩ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ተወካዮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አምባሳደር መሀመድ ድሪር ተናግረዋል ።
ከዚህ ባለፈም የድሬዳዋ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት እና የወረዳ ህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ያስፈልጋል የሚሏቸውን እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን የያዙ አጀንዳዎችን በህዝባዊ ውይይት የሚሰበሰብበት ወሳኝ ምእራፍ መሆኑን አምባሳደር መሀመድ ድሪር ገልፀው በዚሁ መድረክ ላይም ከአንድ ሺህ በላይ ተወካዮች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ነው አምባሳደር መሀመድ ድሪር ያስታወቁት ።
ከፊታችን ሰኞ አንስቶ ለተከታታይ ሰባት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር በሚካሄደው የምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይም ሀገራዊ ፋይዳን በመረዳት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባም ነው አምባሳደር መሀመድ ዲሪር ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያስታወቁት ።


