የኮሪደር ልማት በዋናነት የዋና ዋና መንገዶች አካባቢን የማልማት እንዲሁም ፅዱና ውብ የማድረግ ስራ የሚሰራበት ፕሮጀክት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ

በድሬደዋ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዓላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ከወረዳ 02፣ ከ03 እና 04 ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬደዋን ብልፅግናና ዘመናዊ ከተማነት በላቀ መልኩ ለማስቀጠል በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የኮሪደር ልማት በዋናነት የዋና ዋና መንገዶች አካባቢን ማልማት እንዲሁም ፅዱና ውብ የማድረግ ስራ የሚሰራበት ፕሮጀክት መሆኑን ተናገረዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱንም በአስተዳደሩ ተግባራዊ ለማድረግ ከዚህ ቀደምም ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን አቶ ሀርቢ በማንሳት የዛሬው የውይይት መድረክ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ሀርቢ አያይዘውም የልማት ስራዎች የሚሰሩት ለማህበረሰቡ በመሆኑ በአስተዳደሩ የኮሪደር ልማትን ለማስጀመር ከማህበረሰቡ ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬው የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ሀርቢ የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ ለሚሰሩ ማንኛውም ስራዎች በነቂስ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ሁሉም የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ድሬዳዋን ለማልማት አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

በተመሳሳይም ከመልካ አካባቢ ነዋሪዎች ጋርም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዓላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ውይይቱ ተደርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *