በአስተዳደሩ ለሚንቀሳቀሱ የመንግስት ተሽከርካሪ ሹፌሮች በተሻሻለው የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ
አሽከርካሪዎች መሰል መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሶስተኛ ቀኑን በያዘውና በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችን በተሻሻለው የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ላይ የግንዛቤ ለማስጨበጫ የተዘጋጀው መድረክ ማጠናቀቂያውን አድርጓል። በመድረኩ የደንቡ መሻሻል ባስፈለገባቸው ነጥቦችና በደንቡ የተካተቱ የጥፋት እርከኖች ላይ ለመንግስት ተሽከርካሪ ሹፌሮች ማብራሪያ ሰቷል። የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግም አሽከርካሪዎች ባነሱት ሀሳብ ተሽከርካሪዎቻችን በወቅቱ ሰርቪስ አይደረጉም ብልሽት ሲገጥማቸው ወቅታዊ…


