መንግስታችን የቅርሶችን እድሳት እና የኮሪደር ልማት ስራን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሀገራችን ከተሞችም በመጀመር ከተሞቻችንን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።
እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳዱን የጅማ ከተማ እና የአካባቢውን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ወደር በማይገኝለት ተሳትፏቸሁ ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን በማስቻላችሁ እና ላሳያችሁን ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባቹሃል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


