የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ የማስፋፊያ ስራና ተያያዥ ጉዳዮችን በአስተዳደሩ እና በፊደራል አመራሮች ተጎበኘ

የፋብሪካው ማስፋፊያ ከዚህ ቀደም ከብክለት ጋር ተያይዞ ይነሱበት የነበሩ ቅሬታዎች ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡

የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ በአመት የማምት አቅሙን ወደ ስድስት መቶ ኩንታል ከፍ የሚያደርግ ማስፋፊያ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

በኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁም በድሬደዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃርቢ ቡህ የተማራ ቡድን የፋብሪካውን የማስፋፊያ ስራና ተያያዥ ጉዳዮችን በመጎብኝት ከፋብሪካው አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚንስቴር የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚደግፉ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በመከታተልና በመደገፍ የሚገጥሙ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲቀረፉ የማድረግ ስራ እንደሚከናወን የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንሰትር ደኤታው አቶ ሚሊዮን በወቅቱ ገልጸዋል፡፡

ድሬደዋ የሃገር ሃብት የሆኑ ግዙፍ ፋብሪካዎች መገኛ መሆኗን የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ በአስተዳደሩ ከሚገኙ መሰል ፋብሪካዎች አንዱ መሆኑን የገለፁት ሚንስትር ደኤታው በፋብሪካው እየተከናወነ የሚገኝው የማስፋፊያ ግንባታ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ፋብሪካው በምርት ሂደት ከብክለት ጋር ተያይዞ ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚነሳበትን ቅሬታዎች ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በመሆን በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ መሰራትእንደሚገባው ከፋብሪካው አመራሮች ጋር ከስምምነት ተደርሶ እንደነበር በጉብኝታቸውም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ሚንስትር ደኤታው አረጋግጠዋል።

የፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪሃጅ ዶክተር አብዱጀባር አብዱሰመድ ፋብሪካው ከጊዜ ወደ ጊዜ የአመራረት ሂደቱን ለማዘመን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፋብሪከው ቀደም ሲል ክሊንከር ብቻ ሲያመ፨መርት መቆየቱን አሁን እየተገነባ ያለው ማስፋፊያ ሲሚንቶን ወደማምረት እንዲገባ እንደሚያስችለው የምርት መጠኑንም በአመት ከአራት መቶ ሺህ ኩንታል ወደ ስድስት መቶ ሺህ ኩንታል ከፍ እንዲል እንደሚያደርገው ምክትል ስራ አስኪሃጁ ጠቁመዋል።

ምርትን ከማሳደግ በተጨማሪም ሲደርስ የነበረውን የብክለትና የብክነት ችግር በማስቀረት የተሻለ አሰራርና አመራረት ሂደት እንዲኖር ያግዛል ብለዋል።

ፋብሪካ በሚያደርገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚገጥሙ ችግሮች እንዲቀረፉ የድሬደዋ አስተዳደር በቅርበት ሆኖ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝ በዚህም በፋብሪካው ስንም ከፍ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንደሚወዱ ዶክተር አብዱ ጀባር ገልፀዋል።

በዳግማዊ ፍቃዱ

ፎቶ፦ቴድሮስ ልኡልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *